Prophacy
- Paulos D. G.
- Jul 1, 2016
- 1 min read

አንድ ሰው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኙ ተቀብሎ ዳግም ከተወለደ በኋላ ሊጠፋ የሚችልባቸው መንገዶችአሉን?
አዎ! አንድ አማኝ በሚኖረው መንፈሳዊ ሂይወት ወደኋላ ቢያፈገፍግ ወይም ጌታን ቢክድ ሊጠፋ ይችላል፡፡ ጌታን መካድ በሁለት መልኩ ሊገለጥ ይችላል፡
ሀ. በአንደበቱ ጌታን አመልካለሁ እያለ በድርጊት ግን ከክርስቶስ ዶክትሪን ጋር የሚጋጭ ተግባር እየፈጸመ ቢቀጥል
"የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።" 2ኛ ጢሞ. 3፡5
ለ. በቀጥታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም መሲህ አይደለም፣ የእግዚአብሄር ልጅ አይደለም፣ ጌታ ወይም አምላክ አይደለም ብሎ ቢክድ ከእውነተኛው የወይን ግንድ ላይ ተቆርጦ ሊጣል ይችላል፡፡
"እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ጭከና ተመልከት፤ ጭከናው በወደቁት ላይ ነው፥ በቸርነቱ ግን ጸንተህ ብትኖር የእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ላይ ነው፤ ያለዚያ አንተ ደግሞ ትቆረጣለህ።" ሮሜ 11፡22
"ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።" ዕብ. 10፡38
"ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ
ይሰጣችኋል፤" ዮሐ. 14፡15-16
"እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።" ማቴ.24፡ 13
Comments